Additional Information

Additional Information

Account Navigation

Account Navigation

Currency - All prices are in AUD

Currency - All prices are in AUD
 Loading... Please wait...
Africa World Press & The Red Sea Press

Malet Yemifeligew by Muhammed Hassen

$29.95

Malet Yemifeligew by Muhammed Hassen

$29.95
SKU:
978-1-56902-646-5
Quantity:
Share

Product Description

ማለት የምፈልገው

ሙሐመድ ሐሰን

ማለት የምፈልገው ብዙ ጉዳዮችንና ጥያቄዎቸን ካሁን በፊት እነርሱን በተመለከተ፣ ከነበሩት ትርጓሜዎችና አመለካከቶች የተለዩ ጥልቅና ጥብቅ በሆነ ጥናት ላይ የተመሰረቱ ትንታኔዎች ውብ በሆነ አቀራረብ ለግሶልናል። ኢትዮጵያ እንዴት ነው እንደ ሀገር የተገነባችው? ይህች ረጅም ታሪክ ያላት አገር ለምን ባሁኑ ጊዜ ሗላ ቀር ሆና ትገኛለች? የዕውቀት ዋና ቁምነገርና በሀገር ግንባታ ሂደት ያለው ድርሻ ምንድነው? ካለፉት ስህተቶቻችን እንዴት ነው መማር ያልቻልነው? መገዳደል፣ ሴራ፣ ቅናት፣ ተንኰልና ሌሎች ስነልቦናዊ ድክመቶቻችን እስካሁን ከሚያሰቃዩን ችግሮች ጋር የሚዛመዱት እንዴት ነው? ከዚህ አኳያ በአገሪቱ የነበሩትም ይሁኑ አሁን ያሉት መንግስታት የሚገለፁት እንዴት ነው? ባለፈው አንድ ዘመን የታዩት መንግስታት፡ ማለት፡ የአፄ ሃይለስላሴ የደርግና የኢህአዲግ፡ ተመሳሳይነታቸውና ልዩነታቸው ምንድነው? ’ያ ትውልድ’ ተብሎ የሚጠራው ረድፍ ጥንካሬዎቹና ድክመቶቹ ምንድናቸው? እነዚህንና ሌሎች ጥያቄዎችን በጥልቀት በመተንተን ደራሲው ለብዙዎቻችን አዲስ የሆኑትን ትርጓሜዎች ግልፅና ቀጥታ በሆነ ቋንቋ አቅርቦልናል፡፡ ከነዚህ ጥያቄዎች ጋር በተያያዘ መፅሃፉ ስለክርስትናና እስልምና ዝምድና በኢትዮጵያ በጥልቀት ይመረምራል፣ በዚህ ምርምር ላይ የተመሰረተ ስለ አፄ ምንሊክ አስተዋይነትና ስለ ልጅ ኢያሱ ብሄረተኛነት አሳማኝ የሆነ አዲስ ትረካ ተገልፀዋል፡፡ ተፈሪ መኰንን ለስልጣን ብለው እንዴት የአውሮጳውያን ዕቅድ እንዳመቻቹ፣ አውሮጳውያኖቹም ለጥቅማቸው ሲሉ ተፈሪን በስመ ተራማጅነት በማሰቀደም እንዴት በኢያሱ ላይ እንደዘመቱ መፅሃፉ ያስረዳናል፡፡ ይህ መፅሃፍ ያሁኑ ችግራችንን በጥልቀት ለመረዳት፣ ብሎም ብቁ መፍትሄ ለማፈላለግ በአመርቂነት የሚረዳ ትልቅ ፀጋ ነው፡፡ መፅሃፉ ብዙ የተለፋበት፣ ዕውነትን የተማመነ ቀጥተኛና በመንፈሳዊ ወኔ የጐለበተ ስራ ነው፡፡ ልበሙሉነት እውነትን ህይወት ይሰጣታል፡፡ ከአንድ ምሁር የሚጠበቅ ታታሪነት ቀጥተኛነትና ልበ ሙሉነት በዚህ በዶክተር መሐመድ መፅሃፍ ተንፀባርቀዋል፡፡
ፕሮፈሰር ተስፋፅዮን መድሃኔ
ብረመን ዩኒቨርስቲ፣ ጀርመን

ሙሐመድ ሐሰን፣ ፒኤችዲ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፣ የአፍሪካ ጥናትና ምርምር ተቋም መምህር ናቸው። የዚህ ተቋም መስራችና የመጀመሪያው ዲሬክተርም ነበሩ። ዶር ሙሐመድ በዚሁ ዩኒቨርሲቲ ጆርናሊዝምና ኮሚኒኬሽን ትምህርት ክፍልም አስተምረዋል። ወደኢትዮጵያ ከመመለሳቸው በፊት የማስተር ትምህርታቸውን በተከታተሉበት በሩር ዩኒቨርሲቴ ቦኹም በመምህርነት እና የውጭ ሐገር ተማሪዎች አማካሪም በመሆን ሰርተዋል፡፡ በተጨማሪም በተለያዩ የጀርመን ተቋማት ለምሳሌ በአምባሲ፣ በጂ.አይ.ዜድ፣ በሃይማኖት ተቋማትና በሌሎችም፣ ጀርመናውያን ወደ ኢትዮጵያ ከመሄዳቸው በፊት ተገቢ ሥልጠና እንዲያገኙ በማድረግ ከአስራ አምስት ዓመት በላይ ሰርተዋል፡፡

CATEGORY

ለታሪክ፣ ፖለቲካ፣ ታሪክ/አፍሪካ/ Memoir, Autobiography, political history/AFRICA

PUBLICATION YEAR 

TRIM SIZE

 6" X 9"

PAGE COUNT

320

Product Reviews

Find Similar Products by Category