Categories
Categories
Authors
Authors
NIGIST FURA: Beafe Tarik Lay Yetemeserete Liboled/QUEEN FURA: An Amharic Novel, by Teshome Birhanu
NIGIST FURA: Beafe Tarik Lay Yetemeserete Liboled/QUEEN FURA: An Amharic Novel, by Teshome Birhanu
Product Description
Queen Fura was a legendary ruler of the Sidama people of the Southern part of Ethiopia. She is known in the legend for having set up an administration dominated by women. It is said that in her administration men suffered injustice, humiliation, and malicious treatment. They were considered as second-class citizens. Although there is no historical record on the reign of Queen Fura, the legend is still popular and fresh in the minds of the Sidama people. When men pass the alleged burial place of Queen Fura, they struck the ground with their spear and curse the Queen for the suffering of their forefathers. This is in sharp contrast with women who praise the Queen with songs and visit her shrine/burial place bringing with them sacrifices and offers. This Amharic novel, which is based on a thorough research of the Sidama culture and Queen Fura’s claimed administrative area, presents the Queen as a justice seeking and visionary ruler.
ይህ መጽሐፍ በንግሥት ፉራ አፈታሪክ ላይ የተመሠረተ ልቦለድ ነው። እንደአፈታሪኩ ከሆነ፣ ንግሥት ፉራ በሲዳማ ውስጥ ስመ ገናና እና ታላቅ ንግሥት ነበረች። ይች ታላቅና ስመ ገናና ንግሥት የወንዶችን የበላይነት ሥርዓት አስወግዳ የሴቶችን የበላይነት ለመመሥረት ጥረት ያደረገች፣ በጀግንነቷ ወደር እንዳልነበራት ይነገርላታል። ስለዚች ታላቅ ንግሥት የሲዳማ ዞን አስተዳደር ትኩረት በመስጠት በትውልድ ስፍራዋ በይርጋለም የምርምር ተቋም በስሟ ሰይሟል። በሐዋሳ ውስጥም አደባባይና የጉባኤ አዳራሹ እርሷን ለማስታወስ በሚያስችል መልኩ ተቋቁመዋል። ሆኖም ስለዚች ታላቅ ንግሥት የምናገኛቸው የስነጽሑፍ ሥራዎች ውስን ናቸው፡፡
ፀሀፊው፣ ተሾመ ብርሃኑ ከማል፣ የንግሥት ፉራን ታሪክ በልቦለድ መልክ ከማቀናበሩም በተጨማሪ፣ ዝርዝር አፈታሪኩን ከሌሎች የአለማችን ታላላቅ ነገሥታት ጋር በማነፀፀር በመግቢያው ላይ አቅርቧል። ይህ በራሱ ወደፊት ስለዚች ታላቅ ንግሥት ምርምር ለማድረግ ለሚፈልጉ ጥሩ መረጃ እንደሚሆን አያጠራጥርም። ልቦለዱ የንግሥት ፉራን ታላቅነት ከማሳየቱም በላይ፣ ስለሲዳማ ባህልና ታሪክ ጥሩ ማስተዋወቂያም ነው። ፀሀፊው፣ ንግሥት ፉራ ነበረችበት ስለሚባለው አካባቢ እና ስለሲዳማ ባህል ጥልቅ ምርምር ያደረገ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል።
ተሾመ ብርሃኑ ከማል ለ37 ዓመታት ያህል በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት፣ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን፣ እና በኢትዮጵያ ፕሬስ ኤጀንሲ በጋዜጠኝነት እንዲሁም በተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በሕዝብ ግንኙነት መኮንንነት እና በኮሙኒኬሽን መምሪያዎች ኃላፊነት አገልግሏል። ከአንድ ደርዘን ያላነሱ የሕጻናት መጻሕፍትና የሕጻናት ተውኔቶችን፣ አንድ ዘመናዊ የሕልም መፍቻ፣ የኢማም አሕመድ ኢብራሂም ታሪክ፣ መቻቻልና የዓለም ታላላቅ ሰዎች የሕይወት ታሪክና ጥቅሶቻቸውን አሳትሞ ለንባብ አብቅቷል፡፡ በልዩ ልዩ ዓለም አቀፍና ብሔራዊ ጉባኤዎች ስለሰላም፣ ፍቅርና መቻቻል፣ እንዲሁም ጋዜጠኝነትንና የሕጻናት ስነጽሑፍን በሚመለከት የጥናት ወረቀቶች አቅርቧል፡፡
CATEGORY
Literature, Novel/AFRICA