Additional Information

Additional Information

Account Navigation

Account Navigation

Currency - All prices are in AUD

Currency - All prices are in AUD
 Loading... Please wait...
Africa World Press & The Red Sea Press

LANGUAGE AND IDENTITY IN ETHIOPIA, by Girma A. Demeke/ቋንቋና ነገድ በኢትዮጵያ: የኢትዮጵያ ህዝብ ማንነትና ቅድመታሪክ, ግርማ አውግቸው ደመቀ

$29.95

LANGUAGE AND IDENTITY IN ETHIOPIA, by Girma A. Demeke/ቋንቋና ነገድ በኢትዮጵያ: የኢትዮጵያ ህዝብ ማንነትና ቅድመታሪክ, ግርማ አውግቸው ደመቀ

$29.95
SKU:
9781569025994
Quantity:
Share

Product Description

ይህ መፅሀፍ ስለኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ቤተሰቦቻቸው የታሪካዊ ስነልሳን ጥናት መውሰድ እስከሚችለው የግዜ ገደብ ድረስ በመጓዝ መሰረታዊ መረጃ ያቀርባል። ቋንቋና ተናጋሪው የሚለያይ አይደለምና፣ ከቋንቋዎቹ አንፃር በመነሳት የኢትዮጵያን ህዝብ ማንነትና ቅድመታሪክ ይዳስሳል። የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ተናጋሪዎቻቸው ማንነትን እንዲሁም ቅድመታሪካቸው ላይ በዘመናችን ያሉ ጥናቶች የደረሱበትንና አዳዲስ መረጃዎችን በመያዝ መመርመሩ በቀደምት ስራዎች በስፋት ስለቀረበው ስለቋንቋዎቹም ሆነ ስለህዝቦቹ የትመጣ ወቅታዊ ግንዛቤ እንዲኖረን ያስችላል።

የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ከተወሰኑ ብቸኛ ቋንቋዎች በስተቀር አፍሮኤሽያቲክና ናይሎሰሀራን ከሚባሉ ታላቅ ቤተሰቦች ይመደባሉ። ከተወሰኑ የናይሎሰሀራን ቋንቋዎች በስተቀር ሌሎቹ ለረጅም ግዜ በኢትዮጵያ የነበሩ ናቸው። መፅሀፉ የአፍሮኤሽያቲክ ቋንቋዎች ከኤሽያ በተለያየ ወቅት ወደኢትዮጵያ ገቡ የሚለውን መላምት በስፋት መርምሮ ይህ ስለመሆኑ አሁን ያለው መረጃ ማረጋገጫ እንደሌለው ያሳያል። ከዚህም በላይ በህብረተሰብ መሀከል ስላለ ውህደትና ልዩነት በስፋት ይዘረዝራል።

                                                       ************************************************

በዚህ መጽሐፍ ዶ/ር ግርማ አውግቸው ቋንቋና ነገድ በኢትዮጵያ በሚል ርዕስ የኢትዮጵያን ሕዝቦች ማንነትና ታሪካዊ አመጣጥ ከቋንቋ አንፃር ተንትኖ አቅርቦልናል። መረጃዎች በታሪካዊና ንጽጽራዊ ስነልሳን ዘዴዎች ተቀነባብረው በመቅረባቸው ስለ ኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ተናጋሪዎቻቸው ያለንን ዕውቀት ለማሳደግ በእጅጉ ይረዳል። ቋንቋ የተናጋሪው የመግባቢያ መሳሪያ ብቻ ሳይሆን የማንነት መግለጫ ከሆኑት ሌሎች በርካታ እሴቶች አንዱ መሆኑን በመጽሐፉ በሚገባ ተገልጿል። ቋንቋ የጋራ ታሪክና የአንድነት ማጠናከሪያ መሳሪያ መሆኑንና፣ በአንጻሩ ደግሞ የልዩነት ማጉያ መሳሪያም ሊሆን እንደሚችል ተብራርቷል። ከበቂ መረጃ ጋር አብዛኛዎቹ የኢትዮጵያ ሕዝቦችና ቋንቋዎች ምንጫቸው አንድ መሆኑን እንረዳለን። የተናጋሪዎች ለብዙ ዘመናት ተራርቆ መኖር ከአንድ ቤተሰብ የተገኙ ቋንቋዎችን ሊያለያይ እንደሚችል ሁሉ፣ ለብዙ ዘመናት አብሮ በመኖር የተነሳ ከተለያዩ የቋንቋ ቤተሰቦች የተገኙ ቋንቋዎች ደግሞ በቋንቋ ባህርያትና በሌሎችም እሴቶች እየተመሳሰሉ ሊሄዱ እንደሚችሉ በውል ያስገነዝባል። ከዚህ በፊት ለሕትመት እንዳበቃቸው መጽሐፎች ሁሉ፣ ይህ የዶ/ር ግርማ መጽሐፍም ስለ ማንነታችን፣ ስለ ሥርዓተ ጽሕፈታችን፣ ስለ ቋንቋዎችና ቀበሌኛዎች አሻሚነት በርካታ ንድፈ-ሃሳባዊ ቁምነገሮችን አካቶ ይዟል። በመጽሐፉ ሌሎችም አበይት ጉዳዮች የተተነተኑ ሲሆን፣ ወደፊት ምርምር የሚሹ ሃሳቦችም ተነስተዋል። ይህ መጽሐፍ ቀደም ባሉት ዓመታት ቢታተም ኖሮ ቋንቋን በተመለከተ ለተነሱ ችግሮች መፍትሄ ሰጪ ይሆን ነበር ብዬ አስባለሁ። ሆኖም ቋንቋ ሁለንተና በሆነባት ልሳነ-ብዙ አገራችን የመጽሐፉ አስተዋጽኦ በማንኛውም ጊዜ ጉልህ ነው። ከዚህ በጣም ጠቃሚ መጽሐፍ በተለይ የስነ-ስብዕናና የኅብረተሰብ ሳይንስ ተማሪዎችና ተመራማሪዎች የሚጨብጡት ቁምነገር ብዙ እንደሆነ አምናለሁ። መጽሐፉ በአማርኛ በመጻፉ ደግሞ በተለይ በአገር ውስጥ ተነባቢነቱን በእጅጉ እንደሚጨምረው መገመት ይቻላል።
—ዘለዓለም ልየው፣ ፕሮፌሰር
የስነ-ልሳን ትምህርት ክፍል መምህርና የስነ-ስብዕና፣ ቋንቋ ጥናት፣ጋዜጠኝነትና ኮሚዩኒኬሽን ኮሌጅ ዲን፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

ABOUT THE AUTHOR
ግርማ አውግቸው ደመቀ የስነልሳን እና የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ባለሙያ ናቸው። የምርምር ትኩረታቸው በአብዛኛው የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ታሪክና ስነመዋቅር ላይ ነው። በቅርቡ በእንግሊዝኛ ካሳተሟቸው መፅሀፎች መሀከል የአማርኛ ጥንተ አመጣጥ—ሁለተኛ እትም (2013)፣ ሰዋስዋዊ ለውጥ በሴሜቲክ—የአማርኛ ሰዋስው በዘመን ሂደት (2014)፣ እናየአርጎባ ንግግር አይነቶች/ቋንቋዎች (2015) ይገኙባቸዋል።

CATEGORY
Historical Linguistics, History, Ethiopian Studies/AFRICA

PUBLICATION YEAR
2018

PAGE COUNT
272 Pages

Product Reviews

Find Similar Products by Category