Additional Information

Additional Information

Account Navigation

Account Navigation

Currency - All prices are in AUD

Currency - All prices are in AUD
 Loading... Please wait...
Africa World Press & The Red Sea Press

ሱታፌ ከበደች ተክለአብ/ Kebedech Tekleab

$19.95

ሱታፌ ከበደች ተክለአብ/ Kebedech Tekleab

$19.95
SKU:
978-1-56902-876-6
Quantity:
Share

Product Description

ሱታፌ
ከበደች ተክለአብ

“ሱታፌ” የተሰኘው የከበደች ተክለአብ መጸሓፍ የደራሲዋ ሁለተኛ የግጥም መድበል ነው። መጸሓፉ ውስጥ የተካተቱት ግጥሞች በሙሉ የተጻፉት ደራሲዋ ለአስር ዓመታት ያህል በሶማሊያ እስር ቤቶች ታስራ ከተለቀቀች በሁዋላ በአሜሪካን አገር በምትኖርበት ወቅት ነው። የእሥሩ ህይወቷ በእሷና በዓለም መሃል የፈጠረውን ትልቅ ክፍተት ለማጥበብ በምትሰራበት ወቅት የተገነዘበቻቸው እውነታዎች “ሱታፌ” ውስጥ ለተካተቱት ግጥሞች ሃሳብ-ጫሪ ሆነዋታል። ግኝትና እጦቶች፣ አፍቅሮትና ቅብፀቶች፣ ጦርነትና ሰላሞች፣ መፈናቀልና መደላደሎች ከግላዊ እና ከዓለም-አቀፋዊ ምናቦች ጋር ተጣምረው ሰው ላይ በሚያደርሱት ጉዳት አንጻር ተመልክታቸዋለች። ግጥሞቹ ገጣሚዋ እጅግ አዳጋችና እንዲሁም መልካም ክስተቶችን ጠለቅ ብላ የመረመርችባቸው ውስጣዊ የህሊናዋ ውይይት ነፀብራቆች ናቸው።;

Kebedech Tekleab's book "Sutafe"  is the poet's second book of poetry. All the poems in the book were written while Tekleab was living in the United States of America following her release from ten years of imprisonment in Somalia's concentration camps. While struggling to relink her connectedness to the world that had been broken for years, the poet's observation of life became influences for the poems included in "Sutafie". Losses and achievements, love and despair, war and accord, displacement and settlement, intertwined with the global and the personal are explored by observing their impacts on individuals, including her. The poems are Tekleab's inner dialogue with herself on challenging and benign issues.


በሱታፌ ሰው መሆንና ገጣሚነትን አይቻለሁ። ፍቅር-ጥላቻን፣ ሀዘን-ደስታን፣ በአጠቃላይ ውስጣዊ ስሜትን በቃላት ነፍስ ዘርቶ እንዲሰማና እንዲዜም ግጥም የማድርገ ትልቅ ሀይል አለው። ገጣሚ ለመሆን ደግሞ ተሰጥዖ ያስፈልጋል። ታላቅ ገጣሚ ለመሆን ከዚህም በላይ ጥረት ይጠይቃል። በንባብና በልምድ የካበተ እውቀት ከማዳበር ባሻገር ለክፋት ሳይሆን የተባ ብዕርን ለሰብአዊነት ማዋልን ይሻል። በሱታፌ ከቋንቋ ውበት ጀርባ የሰብአዊነት ጥግ ይለካል። ህጋዊ ሽፋን ተሰጥቷቸውም ይሁን ሳይሰጣቸው በሰው ልጆች ላይ የሚደርሱ በደሎች፣ ሰቆቃዎችና ግፎች ለሚሰማቸው ሁሉ፣ ሱታፌ አፍ ሆኗቸዋል ማለት ይቻላል። ሰው መሆን ከራስ ስሜትና ፍላጎት አልፎ ለሌላው መቆርቆርና ጠበቃ ሆኖ መገኘትን ይጨምራል። ይህ በሱታፌ ይታያል። ከበደች በኢትዮጵያ የስነግጥም ታሪክ ትልቅ ቦታ የሚሰጣት አለምክንያት አይደለም።
—ግርማ አውግቸው ደመቀ፣ ዶ/ር  የስነልሣን ባለሙያ


ከበደች ተክለአብ ከበደች ተክለአብ በሲቲ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ኒውዮርክ ውስጥ ነባር የሥእል አሶሲየት ፕሮፌሰር ነች።የመጀመሪያው የከበደች ተክለአብ የግጥም መጽሓፍ የታተመው እንደ አውሮጳ አቆጣጠር 1990 ሲሆን በ2020 እንግሊዛዊው ክሪስ በኬትና ዓለሙ ተበጀ አሰባስበው በጻፉት "Songs We Learn From Trees: An Anthology of Ethiopian Amharic Poetry,"  የግጥም መጽሓፍ ወስጥ ግጥሞችዋ ተካተዋል። በ2023 ህንድ አገር በታተመው "Soul Spaces: Poems on Cities, Towns & Villages";  በተሰኘው የግጥም ስብስብ መጽሓፍ ውስጥም ግጥሞቿ ታትመዋል። “Poetry International” የተሰኘው ድረ-ገጽ በንግሊዝኛ የተተረጎሙ ግጥሞቿን በነዋሪነት ሲያሰፍር የእንግሊዝ አገሩ “The Manchester Review” እንዲሁም የኒውዮርክ ዩኒቨርሲቲው “Washington Square” የተሰኙት ታዋቂ ጆርናሎችም ግጥሞቹዋን አቅርበዋል።


ከበደች ተክለአብ በሥእል ሞያዋም በታወቁ ሙዚየሞችና የሥእል ተቋሞች ውስጥ በግልና በህብረት የሥእል አውደ- ራእዮች አቅርባለች። ከነዚህ ውስጥ ጥቂቶቹ በዋሽንግተን ዲ.ሲ. የሚገኘው “The Museum of African Art, Smithsonian Institution” ቺካጎ የሚገኘው “Holocaust Museum” ስቫና ጆርጂያ የሚገኘው “Maritime Museum” የፍሎሪዳው “Museum of Art in Orlando” እንዲሁም የኒውዮርኩ ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲት እና የዲ.ሲ.ው አሜሪካን ዩኒቨርሲቲ ሚዚዮሞች ናቸው።


Kebedech Tekleab is a tenured Associate Professor of Art at the City University of New York
(CUNY.) She is a painter, a sculptor, and a published poet. She has been featured in Poetry International, The Manchester Review, Washington Square, and others. Kebedech Tekleab has had solo and group exhibitions in such venues as the Smithsonian Institution in Washington DC, The Holocaust Museum in Chicago, Illinois, Maritime Museum in Savannah, Georgia, Orlando Museum of Art in Orlando, Florida, and recently, at the American University Museum, at Columbia University and in an international exhibit in Greece.

TRIM SIZE: 5.5 X 8.5”

PAGE COUNT: 128

PUBLICATION DATE:  2024

 

 

Product Reviews

Find Similar Products by Category