Additional Information

Additional Information

Account Navigation

Account Navigation

Currency - All prices are in AUD

Currency - All prices are in AUD
 Loading... Please wait...
Africa World Press & The Red Sea Press

የት ነው? ከበደች ተክለአብ/ Kebedech Tekleab

$19.95

የት ነው? ከበደች ተክለአብ/ Kebedech Tekleab

$19.95
SKU:
9781569028582
Quantity:
Share

Product Description

‹‹የት ነው?›› ደራሲዋ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር (እአአ) በ1970ዎቹ መጨረሻ በተካሄደው የኢትዮጲያና ሶማሊያ ጦርነት ሳቢያ በወጣትነትዋ በሶማልያ ውስጥ ለአስር አመታት በታሰረችበት ወቅት የተፀፉ ግጥሞችን የያዘ መድብል ነው። ግጥሞቹ በእስር ላይ እያለች የተገነዘበቻቸውን ሃቆች የሚያመለክቱ የጥበብ ስራዎች ናቸው። በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጲያውያን ሲቪል ወንዶች፤ ሴቶችና ህጻናት እንዲሁም የጦር ምርኮኞች በኖሩባቸው ከአለም አይን የተሰወሩ ድብቅ የግዳጅ ስራ ካምፖች ውስጥ የተስተዋሉ እና የተኖሩ ልምዶች የወለዷቸው እነዚህ ግጥሞች የእስረኛውን ህብረተሰብ ኑሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ያሳዩ ገርበብ ያሉ መስኮቶች ናቸው። ቀደም ሲል በመድሃኒት ፓኮ ልጣጭ ላይ በህቡእ የተጻፉት ስብስቦች ገጣሚዋ ከእስር በተመለሰችበት ወቅት ባዲስ አበባ ከተማ በ1989 እአአ ለመጀመሪያ ጊዜ ታተሙ። ይህ ሁለተኛ እትም በመጀመሪያው እትም በሳንሱር ምክንያት ያልተካተቱ ግጥሞችንና አዲስ መግቢያ ይዟል።

Kebedech Tekleab’s poetry book “Yet Newe?” was written during the poet’s ten years of imprisonment in Somali labor camps as a young girl because of the Ethio-Somali war in the late 1970s. The poems were direct accounts of her lived experiences in the prison camps, where thousands of civilian men, women, children, and war prisoners were subjected to forced labor in the camps that were hidden from the world. Those poems became the first window that cracked open the lives of the prisoners so the world could see a glimpse of them. The first edition of the collection that was initially written in hiding on peelings of medicine packages was published in Addis Ababa, Ethiopia, upon her repatriation in 1989.

                                         ********                                        

ከበደች በልጅነቷ የ11 ዓመት ስደት፣ ግዞትና ወህኒ መክፈልቷን በሥነ-ግጥም ውስጣዊ ብርሃኗ ተቋቋመችው። ይህ ነው የቅኔ ብዕር መክፈልቷና ሚስጥሯ። ከመከራ ሕይወቷ ውስጥ በሥነ-ግጥም ብዕሯ እየታዘለች የሱማሌ ሕዝብን አዲስ ፍቅር ዳሰሰችበት፤ ታቀፈችበት እንጂ፣ የኢትዮጵያንና የሱማሌ ሕዝብን የባህል ድልድይ ቀመረችበት እንጂ፣ በወህኒ ዕድሜዋ የምሬት ባህር አልሰጠመችም።

—ገጣሚ ፀጋዬ ገብረ መድህን

የከበደችን ስራ የተዋወቅኩት በታተመበት ዘመን አካባቢ ይመስለኛል። ሰፊ ሽፋን ተሰጥቶት ማስታወቂያ በወቅቱ መሰራቱን ባላስታውስም፣ ከሶማሊያ ከረጅም እስር በኋላ የወጣች ደራሲ የፃፈችው የግጥም መድበል እንዳለ ወሬው በስፋት ተሰራጭቶ ከእኔና ከወዳጆቼም ዘንድ ደርሶ ነበር። መፅሀፉን መልሼ ያገኘሁት ከአንድ አራት ዓመት በፊት ነው። እንደአዲስ ማንበብ ብቻ ሳይሆን፣ ከአጠገቤ እንዳይርቅ አስቀምጬ ስነጽሁፍ ባማረኝ ቁጥር ደጋግሜ ከማነባቸው ጥቂት ሥራዎች ውስጥ አንዱ ሆኗል። የከበደች መፅሀፍ በኢትዮያ የስነጽሁፍ ታሪክ የራሱን አሻራ እንዲተው ያደረገው ከቋንቋው ውበት ባሻገር በመከራ ዘመን የተፃፈ የሰው ልጅን ጥልቅ ስነልቦና የሚመረምር መሆኑ ይሰማኛል። መፅሀፉ ወገኖቻችን በሶማሊያ እስር ቤት ያሳለፉትን የመከራ ዘመን የምናይበት መስታወትም ነው።

—ግርማ አውግቸው ደመቀ፣ ዶ/ር

የስነልሣን ባለሙያ

ከበደች ተክለአብ ገጣሚ፤ ተርጉዋሚ እና ሰአሊ ናት። እንዲሁም በኒውዮርክ ከተማ በሚገኘው ዘ ሲቲ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ኒውዮርክ ኩዊንስቦሮ ኮምዩኒቲ ኮሌጅ ውስጥ ነባር አሶሲየት የስእል ፕሮፌሰር ናት።

Kebedech Tekleab is a poet, translator, painter, and sculptor. She is also a tenured Associate Professor of art at the City University of New York (CUNY) Queensborough Community College.

 

CATEGORY

Amharic Poetry/AFRICA  World Rights

TRIM SIZE 5.5 X 8.5”

PAGE COUNT 122

Product Reviews

Find Similar Products by Category