Additional Information

Additional Information

Account Navigation

Account Navigation

Currency - All prices are in AUD

Currency - All prices are in AUD
 Loading... Please wait...
Africa World Press & The Red Sea Press

ZEMEN, THE ETHIOPIAN CALENDAR: History and Its Social Evolution, Names of Days & Months, by Girma Demeke/ዘመን አቆጣጠር፣ የቀናትና የወራት ስያሜ

$29.95

ZEMEN, THE ETHIOPIAN CALENDAR: History and Its Social Evolution, Names of Days & Months, by Girma Demeke/ዘመን አቆጣጠር፣ የቀናትና የወራት ስያሜ

$29.95
SKU:
9781569024324
Quantity:
Share

Product Description

This Amharic book discusses the Ethiopian civil calendar in relation to world major calendars and the calendars of ancient civilizations in their historical context. It considers a wide variety of issues including the sociocultural situations and socioeconomic factors of the society that created them. The book also examines names of days and months in Ethiopian languages from the perspective of historical linguistics.

በዚህ መፅሀፍ የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር እንዲሁም የቀናትና የወራት ስያሜዎች ተቃኝተዋል። በእነዚህ ነጥቦች ዙርያ፣ የተሻላ ግንዛቤና አጥጋቢ መልስ ለማግኘት የቅርብ ምስራቅ ሀገራትና የግብፅ የዘመን አቆጣጠሮችና የቀናትና የወራት ስያሜዎችም በንፅፅር ቀርበዋል። ኢትዮጵያ ከነዚህ ሀገራት ጋር ከረጅም ግዜ ጀምሮ ግንኙነት ነበራት። በዘመን አቆጣጠር ረገድ የማይታለፉት የአውሮፓዎቹ የጁሊያን አቆጣጠር እና የግሪጎሪያን አቆጣጠርም ተዳሰዋል።
    
ይህ መፅሐፍ ከግዜ ፅንሰሀሳብ ጋር የተያያዙትን በየቀን ውሎዎች የምንኖራቸውን የባህላችን አካልን በመዳስስ ጥልቅ ትንታኔ በማድረጉ ጠቀሜታው ለስነፈለክ፣ ስነመለኮት፣ ስነልሳን፣ ታሪክ እና ስነሰብ ተመራማሪ/ተማሪ ብቻ ሳይሆን እውቀትን ለሚሻ ሁሉ ነው።
—ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሐቅ፣ ከመፅሀፉ ቀዳሚቃል የተወሰደ

የግርማ መፅሀፍ አቆጣጠርን እንዳለ ማቅረብ ብቻ ሳይሆን በየነጥቡ በጥልቀት መሄድ ለሚፈልግ ጠቃሚ መረጃዎችንም በዝርዝር ይጠቁማል። ይህ መጽሐፍ የኢትዮጵያን ሲቪል የዘመን አቆጣጠርን ብቻ ሳይሆን ዘርፈ-ብዙ መረጃዎችን የያዘ ሰፊ ጥናት ነው።
— ፕሮፌሰር አበበ ዘገየ፣ ከመፅሀፉ ቀዳሚቃል የተወሰደ

የዶር. ግርማ መፅሀፍ የግዜ ፅንሰሀሳብ እንዴት እንደተደራጀ ከማሳየቱም በላይ፣ የቀናትና የወራት ስያሜዎች ላይ ከታሪክ አንፃር የቀረበው ትንታኔ፣ የተለያዩ ህብረተሰቦችን ማህበረ-ባህላዊ  እውቀት ያገናዘበ ነው። መፅሀፉ የአለም የተለያዩ አቆጣጠሮችን እና እነዚህን አቆጣጠሮች የፈጠረው ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ አውድ ላይ ስላለን እውቀት ብዙ ነገር ይጨምርልናል።
— ዶር. ደበላ ጎሹ፣ ከመፅሀፉ ቀዳሚቃል የተወሰደ

ይህ ድንቅ ትምህርታዊ ሥራ፣ ላለን እውቅት ተጨማሪ የሚሆን፣ አስተሳሰባችንን የሚያሰፋ፣ እና ግንዛቤያችንን የሚያዳብር፤ እንዲሁም፣ በበርካታ ነጥቦች ላይ ደግሞ ተመራማሪዎች ጥናት እንዲያደርጉ የሚጋብዝ ነው።  
— ፕሮፌሰር የእብዮ ወልደማርያም፣ ከመፅሀፉ ቀዳሚቃል የተወሰደ

ግርማ አውግቸው ደመቀ የስነልሳን እና የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ባለሙያ ናቸው። የምርምር ትኩረታቸው በአብዛኛው የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ታሪክና ስነመዋቅር ላይ ነው። በቅርቡ በእንግሊዝኛ ካሳተሟቸው መፅሀፎች መሀከል የአማርኛ ጥንተ አመጣጥ—ሁለተኛ እትም (2013)፣ ሰዋስዋዊ ለውጥ በሴሜቲክ—የአማርኛ ሰዋስው በዘመን ሂደት (2014)፣ እና የአርጎባ ንግግር አይነቶች/ቋንቋዎች (2015) ይገኙባቸዋል።

CATEGORY
Historical linguistics, Afroasiatic, Calendar/AFRICA

Product Reviews

Find Similar Products by Category