Categories
Categories
Authors
Authors
ትውስታዎቼ: ስለመሬት ይዞታና የተለያዩ ፓለቲካዊና አገራዊ ጉዳዮች በዓለምአንተ ገብረሥላሴ PB
Product Description
የመፅሀፉ ይዘት የሚያተኩረው ያለፍኩባቸውን፤ የተሳተፍኩባቸውን እና የታዘብኳቸውን የግል ትውስታዎች ነው። "ትውስታዎቼ " በአፄው ዘመን የነበረውን የመሬት ሥሪት ከዳሰሰ በኋላ ሥሪቱን ለማስተካከል የተሞከሩና ሳይሳኩ የቀሩ ጥረቶችን ካስታወሰ በኋላ አዋጅ አወጣጥና አፈፃፀም በዝርዝር ያስረዳል። ቀጥሎም የደርግን አገዛዝ ለመጣል ኢህአፓ ባደረገው የትጥቅ ትግል የነበረኝን ተሳትፎና አሜሪካ ከገባሁ በኋላም የኢትዮጱያ ዴሞክራሲያዊ ህብረት ቅንጀትን በመወከል በአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፤ በካርተር ማዕከልና በነጩ ቤተ መንግሥት የነበረኝን ተሳትፎና የታዘብኳቸውን ኩነቶች አካቷል። ከዚያም ወያኔ የቤጌምድርና ስሜን ክፍለሀገርን ህዝብ በጎሣ ለመከፋፈል የወጠነውን ዕቅድ ለማክሸፍ በውጭ ሀገር የሚኖሩ የክፍለሀገሩ ተወላጆች ባድረጉት እንቅስቃሴ የነብረኝን ተሳትፎ ያትታል። በመጨረሻም ኢትዮጵያንና ሱዳንን ለዘመናት ሲያወዛግብ ስለቆየው የድንበር ጥያቄ ከእንግሊዝ ሀገር መዛግብት ያገኘኋቸውን መረጃዎች ዋቢ በማድረግ የድንበሩ ጉዳይ የሱዳን መንግሥት እንደሚለው እንዳልሆነ ለማሳዬት ሞክሯል።
’እጅጉን ያስቸግር የነበረው የመሬት ይዞታን ለማሻሻል ቀደም ባሉት ዓመታት ይካሄዱ በነበሩ ጥናቶች ውስጥ በመሳተፍ፤ ከ1966 ዓ ም አብዮት በኋላ ደግሞ የወጣውን አዋጅ በማርቀቅና ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ወሳኝ አስተዋጽኦ ካበረከቱት ሠራተኞች መካክል አንዱ ይህ ደራሲ ነበር። ይህ ጉዳይ ብዙ ያከራከረ፣ ያፋጀ፣ የወዳጅ መንግሥታትን ትኩረትም የሳበ ነበር። በዚህ ዙርያ የተከሰተውን ሁሉ በቅጡ አስተውሎ ሐቀኛ የታሪክ ምሑራን በሚፈልጉት ዓይነት መመዝገብ ቀላል አይደለም። ከዚህ አንጻር ደራሲው ሃላፊነቱን በሚገባ በዚህ መጽሐፈ ተውጥቷል ለማለት እንችላለን።”
—ተካልኝ ገዳሙ
ዓለምአንተ ገብረሥላሴ በንጉሡ ዘመን ከአዲስ አበባ ዩኒቭርሲቲ በህግ ከተመረቅሁ በኋላ በመሬት ይዞታ ሚኒስቴር የመሥሪያ ቤቱን የህግ ክፍል በበላይነት መርቻለሁ። የገጠር መሬትን የህዝብ ያደረገውን አዋጅ ካረቀቁት ባለሙያዎች አንዱ ስሆን ስለአዋጁ ይዘት ለደርግ አባሎች ስብስባ ገለፃ ያደርግሁትም እኔ ነበርኩ። አዋጁ ከወጣ በኋላ የመሥሪያ ቤቱ ቋሚ ተጠሪ ሆኜ በመሾሜ የደርግን አገዛዝ ተቃውሜ ወደ ትግል ሜዳ እስከወጣሁበት ጊዜ ድርስ የአዋጁን አፈፃፀም በቅርበት ተከታትያለሁ። በስደት ወደ አሜሪካ ከመጣሁ በኋላ በህግ ተመርቄ ለሦስት ዓመታት ፎሊና ላርድነር (Foley and Lardner) በተባለው ትልቅና ዝነኛ የጠበቆች ማህበር ውስጥ በጠበቃነት ሠርቻለሁ።" ከዚህ በኋላ ቨርጂኒያ ግዛት ውስጥ በሚገኘው የዊልያምና ሜሪ ኮሌጅ ለ27 ዓመታት ህግ አስተምሬአለሁ። በአሁኑ ጊዜ በኤሚሬተስ ፕሮፌሰር ማዕረግ በጡሮታ ላይ እገኛለሁ።
Memoir/AFRICA World Rights
TRIM: 5.5x8.5
PAGE COUNT: 278 pp